ኢትዮጵያ ለስደተኞች አካታች የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ዘረጋች፤ የሀገር አቀፍ አገልግሎቶች ተደራሽነትን ያሳድጋል።
News releases
ኢትዮጵያ ለስደተኞች አካታች የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ዘረጋች፤ የሀገር አቀፍ አገልግሎቶች ተደራሽነትን ያሳድጋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (ስ.ተ.አ) አማካኝነት ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ እና ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ለማካተት ተግባራዊ እርምጃ ጀምሯል።
መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለስደተኞች የማመቻቸት ዓላማ ያለው "ፋይዳ" የተሰኘ ልዩ መለያ ቁጥር ዲጂታል መታወቂያ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚኖሩ ስደተኞች እየተሰጠ ነው።
ባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም በስደተኛ መታወቂያ ካርዶች ላይ የሚታተመው “ፋይዳ” ቁጥር፣ ተደራራቢ ምዝገባ እንዳይኖርና ለስደተኞች ከአንድ በላይ መታወቂያ እንዳይሰጥ ያስችላል።